Esat ዱላ ቀረሽ ክርክር የ ጠ ሚ አብይ አህመድን ወንጀል ኤርሚያስ ለገሰ እና አበበ ገላው ዘከዘኩት1
ከመንግሥት በተሠጠው የመንግሥት መግለጫ መወሠድ ያለበት ዕርምት በከፊል!!! አዲሥ አበባን በተመለከተ፡- ከመንግሥት፡- አዲሥ አበባ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚኖሩባት የሁሉም የሆነች ልክ ባህርዳር የሁሉም ኢትዮጵዊ እንደሆነች ግን በአምሃራ ክልል የምትደዳደር፣ ልክ አዋሣ የሁሉም ኢትዮጵዊ እንደሆነች ግን በደቡብ ክልል የምትደዳደር፣ መቀሌ የሁሉም ኢትዮጵዊ እንደሆነች ግን በትግራይ ክልል የምትደዳደር የሚል ዕንድምታ ያለው መሆኑን እና አዲሥ አበባ ደግሞ የሁሉም ኢትዮጵዊ እንደሆነች ግን በ…….(በውሥጣቸው በኦሮሚያ ክልል የምትደዳደር) በፌዴራልም በልዩ አሥተዳደር የምትደዳደር ማለትም ሁለት አሥተዳደር አላት እንደማለት በሚል መልኩ ለመግለፅ ተሞክሯል፡፡ ዕርምት፡- አዲሥ አበባ የሁሉም ኢትዮጵዊ የሆነች የሁሉም ብሔረሠብ ሕዝቦች የሚኖሩባት ነገር ግን ከሌሎች የክልል ከተሞች የምትለይ በራሷ የተማሩ ተወላጆቿ የምትደዳደር የፌዴራል መቀመጫ፣ የአፍሪካ መዲና ሥትሆን የየትኛውም ክልል መቀመጫ ያልሆነች ነች፡፡ እዚህ ጋር ግን ህገ መንግሥቱን በመጥቀሥ የኦሮሚያ ዕንብርትም ናትና ሁለት አሥተዳደር አላት ለማለት መሞከር ሥሕተት ሢሆን ይህም ህገ መንግሥት የኦሮሚያ ዕንብርት የሚለው መሻሻል የሚገባው ያለሕዝብ ይሁንታ የተፃፈ የሕገመንግሥት አንቀፅ ነው፡፡ በርግጥ የኦሮሚያም ሆነ የአዲሥ አበባ አሥተዳዳሮች የኦሮሚያ ተወላጆች ሥለሆኑ የሁለት አሥተዳደር አይነት በአንድ ሥሜት የሚፈልጉትን ለማሥፈፀም ተመቻችቶላቸዋል፡፡ ከመንግሥት፡- የኦዲፒ አመራሮች እና የአዲሥ አበባ አመራሮች የአዲሥ አበባን ዲሞግራፊ ለመቀየር መታወቂያ በመሥጠት እና የሦማሊያ የተፈናቀሉትን 6000 የሚሆኑ ተፈናቃዮች በአዲሥ አበባ ላይ በማሥፈር የተባለው ሥህተት እንደሆነና ይህም አዲሥ አበ...