Esat ዱላ ቀረሽ ክርክር የ ጠ ሚ አብይ አህመድን ወንጀል ኤርሚያስ ለገሰ እና አበበ ገላው ዘከዘኩት1



ከመንግሥት በተሠጠው የመንግሥት መግለጫ መወሠድ ያለበት ዕርምት በከፊል!!!
አዲሥ አበባን በተመለከተ፡-
ከመንግሥት፡- አዲሥ አበባ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚኖሩባት የሁሉም የሆነች ልክ ባህርዳር የሁሉም ኢትዮጵዊ እንደሆነች ግን በአምሃራ ክልል የምትደዳደር፣ ልክ አዋሣ የሁሉም ኢትዮጵዊ እንደሆነች ግን በደቡብ ክልል የምትደዳደር፣ መቀሌ የሁሉም ኢትዮጵዊ እንደሆነች ግን በትግራይ ክልል የምትደዳደር የሚል ዕንድምታ ያለው መሆኑን እና አዲሥ አበባ ደግሞ የሁሉም ኢትዮጵዊ እንደሆነች ግን በ…….(በውሥጣቸው በኦሮሚያ ክልል የምትደዳደር) በፌዴራልም በልዩ አሥተዳደር የምትደዳደር ማለትም ሁለት አሥተዳደር አላት እንደማለት በሚል መልኩ ለመግለፅ ተሞክሯል፡፡
ዕርምት፡- አዲሥ አበባ የሁሉም ኢትዮጵዊ የሆነች የሁሉም ብሔረሠብ ሕዝቦች የሚኖሩባት ነገር ግን ከሌሎች የክልል ከተሞች የምትለይ በራሷ የተማሩ ተወላጆቿ የምትደዳደር የፌዴራል መቀመጫ፣ የአፍሪካ መዲና ሥትሆን የየትኛውም ክልል መቀመጫ ያልሆነች ነች፡፡ እዚህ ጋር ግን ህገ መንግሥቱን በመጥቀሥ የኦሮሚያ ዕንብርትም ናትና ሁለት አሥተዳደር አላት ለማለት መሞከር ሥሕተት ሢሆን ይህም ህገ መንግሥት የኦሮሚያ ዕንብርት የሚለው መሻሻል የሚገባው ያለሕዝብ ይሁንታ የተፃፈ የሕገመንግሥት አንቀፅ ነው፡፡ በርግጥ የኦሮሚያም ሆነ የአዲሥ አበባ አሥተዳዳሮች የኦሮሚያ ተወላጆች ሥለሆኑ የሁለት አሥተዳደር አይነት በአንድ ሥሜት የሚፈልጉትን ለማሥፈፀም ተመቻችቶላቸዋል፡፡
ከመንግሥት፡- የኦዲፒ አመራሮች እና የአዲሥ አበባ አመራሮች የአዲሥ አበባን ዲሞግራፊ ለመቀየር መታወቂያ በመሥጠት እና የሦማሊያ የተፈናቀሉትን 6000 የሚሆኑ ተፈናቃዮች በአዲሥ አበባ ላይ በማሥፈር የተባለው ሥህተት እንደሆነና ይህም አዲሥ አበባ አሁን የደረሠችበት ቅርፅ እና ይዘት 100ዓመት ፈጅቶባታል፤ ሥለሆነም ዶሞግራፊን መቀየር ከባድ ሞሆኑን መገንዘብ እንዳለብን እና ይህቺ ግን ምንም ማለት አደለችም እንደማለት ለመግለፅ ተሞክሯል፡፡
ዕርምት፡- የሆነው ከህግ አግባብ ውጭ ሢሆን “ይቺ ባቄላ ሥታድር አትቆረጠምምና” እንደሚሉት ከወዲሁ ካልታረመ እና ካልቆመ መቀጠሉ እንደማይቀር እና ለእንደዚህ የህግ ክፍተት እንደሚፈጥር ሣይታወቅ ቀርቶ ነው? ሌላው ማን ፈቅዶ ነው የኦሮሞ ሕዝብ ሢፈናቀል አዲሥ አበባ እንድትቀበል ውሣኔ የሚሠጥ፡፡ ኦሮሚያ ከፈለገ በቀሩት የኦሮሚያ ከተሞች ማሥጠጠለል ይችላል፡፡ ያለበለዚያ ደቡብ የሆኑ አዲስ አበባ ላይ የሚገኙ አሥተዳደሮች የጌዲዮን ተፈናቃዮች አዲሥ አበባ ማሥጠለል ይችላሉ፡፡ ለነሡም 6000 ኮታ ሊደርሣቸው ይገባል፡፡ እንዲሁም ከተለያዩ በተለይም ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉትን አምሃራዎች አዲሥ አባባ ላይ ያሉ የአምሃራ አሥተዳደሮች አዲሥ አበባ ላይ ሊያሠፍሯቸው ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ለነሡም 6000 ኮታ ሊያዝላቸው ይገባል፡፡ ማን ከማን ያንሳል፡፡
ከመንግሥት፡- ከአዲሥ አበባ የሚወጡ እና ወደ አዲሥ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የሚገቡ ፍሣሾች አሉ እና የአዲሥ አበባ አሥተዳደር ለኦሮሚያ ክልል ልዩ ጥቅም ልትሠጥ ይገባል፤ የአዲሥ አበባ ህንፃዎች ሢሠሩ አሸዋ እና አፈር በአዲሥ አበባ ዙሪያ ካሉ የኦሮሮሚያ ከተሞች ሢመጡ በአካባቢው ብክለት ሥለነበረ የአካባቢው ሠዎች ታመዋል እና የአዲሥ አበባ አሥተዳደር ለኦሮሚያ ክልል ልዩ ጥቅም ሊሰጥ ይገባል ተብሏል፡፡
ዕርምት፡- ሥለፍሣሽ ከተነሣ ከአዲሥ አበባ ወጥቶ ወደ በአዲሥ አበባ ዙሪያ ባሉ ኦሮሚያ ከተሞች እንደሚገባው ሁሉ ከነሡም ወደ አዲሥ አበባም እንደሚገባ መታሠብ ይኖርበታል፡፡ ሌላው አሁንሥ በነዚሁ በአዲሥ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ ከተሞች እዛው ቤት ለመሥራት እየተቆፈረ አደለም ወይ፡፡ ስለሆነም አሁን እዛው ላለው ሕዝብ ለሚደርሥበት የአየር ብክለት የኦሮሚያ ክልል ለኦሮሚያ ክልል ይክፈለው ሊባል ነው? ትልቅ ሥህተት ነው፡፡ እዛው አፈሩም አሸዋውም ሢወጣ ክፍያ እየተከፈለበት መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ሌላሥ የኦሮሚያ ተሸከርካሮዎች አዲሥ አበባ ላይ እንደ አሸን የአየር ብክለት ሢያደርሡ የኦሮሚያ ክልል ለአዲሥ አበባ ልዩ ጥቅም ይሠጣል ወይ? እነዚህሥ የአዲሥ አባባ ዚሪያ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች ከአዲሥ አበባ በጣም በቅርበት ከመሆናቸው አንፃር የሥራ ዕድል የአዲሥ አበባን ወጣቶች ጥቅም እየተጋፉ በመሆናቸው የኦሮሚያ ክልል ለአዲስ አበባ አሥተዳደር ልዩ ጥቅም ይሠጣል ወይ? ህክምናሥ ቢሆን እነዚህ በአዲሥ አበባ ዚሪያ ከተሞች ያሉ ሕዝቦች ያለብዙ የትራንሥፖርት እና የቤት ኪራይ ወጪ በቅርበት ከአዲሥ አበባ ህክምና ሥለሚጠቀሙ የኦሮሚያ ክልል ለአዲሥ አባባ አሥተረዳደር ልዩ ጥቅም ይሠጣል ወይ? ውሃሥ ቢሆን ድንበሩ አካባቢ ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ውሃ አንዱ ጋር ሢጠፋ ከሌላው ሁለቱም ከድንበር እያለፉ አንዱ ከአንዱ ውሃ ሣይጠቀሙ ቀርተው ነው? በውሃው ግድቡሥ እነሡም አብረው እየተጠቀሙ አደል ወይ? አዲሥ አበባሥ ምርት ከዙሪያ ካሉት ከተሞች ብቻ ነው እህል እና አትክልት የምታገኘው? እንደውም በአይሡዙ ከተለያዩ ክልሎች ነው የሚመጣው፡፡ ደሞሥ የአዲሥ አበባ ሕዝብ ገንዘብ ከፍሎ እኮ ነው የሚገዛው፤ በነፃ አደለ፡፡ እነዚህ በአዲሥ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞች ከቅርበት አንፃር ሠፊ ገበያ ከአዲሥ አበባ ሥለሚጠቀሙ ተብሎ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ጥቅም ለአዲሥ አበባ አሥተዳደር ይሠጣል? አፋር፣ ሶማሊ እና ጋምቤላ የሃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥለሌላቸው ተብሎ ለሌላው ክልል ልዩ ጥቅም ይሥጡ ይባላል? ኦሮሚያ የምታመርተውን ምርት በአዲሥ አበባ ኤርፖርት በኩል ነው ለውጭ ገበያ የምትልከው ተብሎ ልዩ ጥቅም ለአዲሥ አበባ ትሥጥ ሊባል ነው? የአባይ መነሻ ጣና ነው ተብሎ ልዩ ጥቅም ሡዳንና ግብፅ ለኢትዮጵያ ትሥጥ ሊባል ነው? ይህ ጥያቄ ደግሞ በአዲሥ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል ብቻ ሣይሆን በሌሎች በአገሪቱ ውሥጥ ባሉ ጠቅላላ አጎራባች ከተሞች ጥያቄው እየተዛመተ አገር ያፈርሣል፡፡ ሥለሆነም ልዩ ጥቅም የሚሉት ፈሊጥ ማብቂያ የሌለው የጅል ተረተረት ነው የሚሆነው፡፡
ከመንግሥት፡- በኮዬ ፈጬ የተገነቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ለወጣላቸው እንዳይሠጣቸው ለጊዜው የቆመበት ምክንያት የቦርደር ማለትም የአዲሥ አበባ እና የኦሮሚያ ድንበር በማለፍ የተሠሩ ስለሆነ ከዛ አካባቢ የተፈናቀሉ ገበሬዎች የሠብአዊ የመብት ጉዳያቸው መታየት ስላለበት በልዩ ኮሚቴ መታየት ሥላለበት ነው ተብሏል፡፡
ዕርምት፡- እንዴ ዕጣውን ያወጣው መንግሥት፣ ቤቶቹን የሠራው መንግሥት ታዲያ እነዚህ ለረጅም ጊዜ በተሥፋ ሢቆትቡ የነበሩ ለዛውም ዕጣ የደረሣቸው ዕጣው ግን አንዴ ከተበላሸ ተመልሦ ሥለማይወጣ የነሡሥ ሠብአዊ መብት እንዲጠበቅ እንዴት አልታሠበም፡፡ መንግሥት የአዲሥ አበባም ሆነ የኦሮሚያ ክልል አሥተዳደሮች ሢሠራ የት ሄደው ነበር ሢያልቅ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት፡፡ ለነገሩ የአዲሥ አበባም ሆነ የኦሮሚያ ክልል አሥተዳደሮች አንድ ብሔር ሥለሆኑ የአዲሥ አበባን ህዝብ ጥቅም እንደ አዲሥ አበቤው ሥሜት እንዲኖራቸው መጠበቅ የሠማይ ላይ ጉም መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ኮሚቴውሥ ለኦሮሚያ ክልል የሚያደሉ በአብላጫ ድምፅ ኦሮሞዎች እንዲያፀድቁት ተብሎ የተዋቀረው ኮሚቴ አዲሥ አበቤውን ፋራ መሥሏቸው ይሆን? ለዚህ ነው የአዲሥ አበባ ሕዝብ ባለው የነፃነት እና የመደራጀት መብቱን ተጠቅሞ በራሡ ተወላጆች እንዲተዳደር የሚያሥተደድረውንም ሠዎች ለሚቀጥለው ምርጫ 2012 ዓ.ም. ከወዲሁ ማዘጋጀት የሚኖርበት እና ይህም መብቱ ማሥፈራሪያ ሊደርሥበት የሚገባ አደለም የሚባለው፡፡ እነእሥክንድር ነጋም ይህን ሃቅ ተረድታችሁ ልትበረቱበት ይገባል፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

Comments

Popular posts from this blog

በአዲስ አበባ ጉዳይ ድርድር የለንም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ጋር ባደረገው ውይይት

የአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጎሹ እንዳላማው እና የአብን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ በወቅታዊ ሃ...