የባለአደራው ጋዜጣዊ መግለጫ ክልከላ-(ራስ ሆቴል) በድብቅ የተቀረፀ Ethiopia: Ethiopis







እና የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግሥት እና የኦነግ መራሹ የዶ/ር አብይ
የኢህአዴግ መንግሥት እንዴት ነው የሚለያዩት????????????
ዴሞክራሢ አለ ወይ??????? በነፃነት የመደራጀት መብት አለ ወይ??????????


ሥለመደራጀት!!!!

እንደሚታወቀው መደራጀት በየትኛውም ሀገር የሚኖር የአንድ ዜጋ፣ የቡድን፣ የማህበር በህግ ያልተከለከለ የሠብአዊ መብት እንደሆነ ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ ተመሣሣይ ዓላማ እና አመለካከት ያላቸው ሠዎች በጋራ በመሆን በመደራጀት ዓላማቸውን ማራመድ በህግ ያልተከለከለ ሠብዓዊ መብታቸውን ሊያሥከብሩ ይችላሉ፡፡ ያም ቡድን ወይም ድርጅት ወይም ፓርቲ ዓላማውን በየትኛውም የሃገሪቱ ክልሎች፣ ዞኖች፣ ወረዳዎች፣ ቀበሌዎች እንዲሁም ከተሞች እየተዘዋወረ ሕብረተሠቡን ተመሣሣይ ዓላማ እና ዓመለካከት እንዲኖራቸው በሠላም እና ህግን ባከበረ መልኩ እንዲሁም በዴሞክራሢያዊ አካሄድ ሕዝቡን ያለምንም ተፅዕኖ የማንቃት እና የማደራጀት በህግ ያልተከለከለ መብቱን ሊያሥጠብቅ ይችላል፡፡ ሕብረተሠቡም ያለምንም ተፅዕኖ የመረጠውን ወይም የፈለገውን ቡድን፣ ድርጅት፣ ማህበር፣ እንዲሁም ፓርቲ በመደገፍ አባል የመሆን፣ የመመረጥ፣ ሥብሠባዎችን የመሣተፍ፣ ሃሣባቸውን በነጻነት የመግለፅ ወዘተ… ዴሞክራሢያዊ መብታቸው እንደሆነ ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ ሥለሆነም አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ አንዳንድ ነገሮችን እያነሣን ሥለመደራጀት ማብራራት ይቻላል፡፡ ለምሣሌ ወሎ በታሪክም ሆነ በህግ የአምሃራ ብሔረሠብ የሆነ እንዲሁም አምሃራዎች የሠፈሩበት ቦታ እንደሆነ እና በአምሃራም አሥተዳደር የሚተዳደር እንደሆነ ቢታወቅም ነገር ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚኖሩበት ቦታ እንደሆነም ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ሥለዚህ እዚህ ሥፍራ ላይ የሚኖሩ የትኛውም ሕብረተሠቦች ተመሣሣይ አመለካከት ያላቸው ለምሣሌ የኦነግን ወይም የኦሮሞን ዘውግ የሚያራምዱ እና የሚደግፉ የወሎ ህብረት ማሕበር በማቋቋም ሊደራጁ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ተመሣሣይ አመለካከት ያላቸው ሕብረተሠቦች ለምሣሌ የአብን ወይም የአምሃራን ዘውግ የሚያራምዱ እና የሚደግፉ የወሎ አምሃራ ወጣቶች ህብረት በማቋቋም ሊደራጁ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም በተመሣሣይ በናዝሬት የሚኖሩ የትኛውም ሕብረተሠቦች ተመሣሣይ አመለካከት ያላቸው ለምሣሌ የአብን ወይም የአምሃራን ዘውግ የሚያራምዱ እና የሚደግፉ ሕብረተሠቦች የናዝሬት አምሃራ ወጣቶች ሕብረት በማቋቋም ሊደራጁ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ተመሣሣይ አመለካከት ያላቸው የትኛውም ሕብረተሠቦች ለምሣሌ የኦነግ ወይም የኦሮሞ ዘውግ የሚያራምዱ እና የሚደግፉ የአዳማ ቄሮዎች ወጣቶች ህብረት በማቋቋም ሊደራጁ ይችላሉ፡፡ በተመሣሳይ በድሬዳዋ፣ በቤንሻንጉል፣ በነቀምት፣ በአሠላ፣ በሻሸመኔ፣ በአዋሣ፣ በወላይታ ሦዶ፣ በአርባ ምንጭ፣ በአምቦ፣ በለገጣፎ፣ በሡሉልታ፣ በበሠበታ፣ በዱከም፣ በቡራዩ፣ በሞጆ፣ በደብረ ዘይት፣ በአለማያ፣ በአሠበ ተፈሪ፣ በጅጅጋ፣ በሃረር፣ በባቢሌ፣ በጅማ፣ በወልቂጤ፣ በበደሌ፣ በመቱ፣ በጋምቤላ፣ በቡታጅራ፣ በቱሉ ቦሎ ወዘተ….. የትኛውም ሕብረተሠቦች እንደሚደግፉት እና እንደሚያራምዱት የዘውግ አውድ ሊደራጁ ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ከዛ በምርጫ በዲሞክራሢ የሚፈልጉትን ፓርቲ በዴሞክራሢያዊ ሥርዓት መርጠው የሚፈልጉትን ለምሣሌ ህገ መንግሥቱ እንዲሻሻል በተለይም የፌዴራሊዝም አከላለል ላይ የድሮውን ሁሉም ብሔረሠቦች ሣይጣሉ በአንድነት የሚኖሩበትን ሸዋ አከላለል በመመሥረት አልያም የአዲሥ አበባን ቦርደር አሁን ያሉ ክልሎች ቢያንሥ እንደ አምሃራ፣ ኦሮሞ እና የደቡብ ክልሎች ድንበር የሚጋሩበት እና የወደብ በር ይሁንታ በነዚህ በሦስቱ ላይ እንዲመሠረት ሆኖ እርሥ በዕርሣቸው የሚከባበሩበት፣ የሚዋደዱበት እና በጋራ አብሮ የመኖር ባህላቸው እንደ በፊቱ የሚመለሥበት ሁኔታ እንዲፈጠር በመረጡት ፓርቲያቸው አማካይነት ፍፃሜ እንዲያገኝ የመደራጀት፣ የመወያየት፣ በነጻነት እና በዴሞክራሢያዊ አካሄድ የሠብአዊ መብታቸውን ሊያሥጠብቁ ይችላሉ!!!!

Comments

Popular posts from this blog

በአዲስ አበባ ጉዳይ ድርድር የለንም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ጋር ባደረገው ውይይት

የአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጎሹ እንዳላማው እና የአብን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ በወቅታዊ ሃ...