Tedy Yesimu Tirguame



መላዕክቶች እኛን ዘወትር ከክፉ የሚጠብቁን፣ የሚረዱን፣ የሚያማልዱን የእግዚአብሔር
ረቂቅ አገልጋዮች ናቸው!!!!!!!!!!!!




ስለመላዕክቶች፡- መላዕክቶች እኛን የሰው ሎጆች ዘወትር ከክፉ ዳቢሎስ እና ጭፍራዎቹ የሚጠብቁን፣ የሚረዱን፣ የሚያማልዱን፣ ፀሎታችንን
ወደ አምላካችን እግዚአብሔር የሚያሳርጉልን የእግዚአብሔር ረቂቅ አገልጋዮች ናቸው፡፡ ለመላዕክቶችም የአክብሮት ስግደት እንደሚገባ፣
እንደሚያማልዱን፣ እንደሚጠብቁን፣ ፀሎታችንን እንደሚያሳርጉልን፣ በዓለም መጨረሻ ጥሩ የሰሩትን ካልሠሩት እንደሚለዩ፣ ረቂቅ እና
ነበልባል እሳት እንደሆኑ ወዘተ…. በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሶ እናያለን፡፡ (ሉቃስ 1፡19) መልአኩም መልሶ፡፡ እኔ በእግዚአብሔር
ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፣ እንድናገርህም ይህችንም የምስራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፡፡ (መፅሐፈ ኢያሱ ወልደነዌ) እርሱም
አይደለሁም፤ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምደር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና፡፡ ጌታዬ
ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው? አለው፡፡ (ኦሪት ዘፍጥረት 19፡1) ሁለቱም መላዕክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥም በሰዶም
በር ተቀምጦ ነበር፡፡ ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፣ አላቸውም፡፡ (መዝሙረ ዳዊት
91:11) በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን
 ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ (መዝሙረ ዳዊት 104:4) መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል።" (የማቴዎስ ወንጌል 4:6) መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።" (የማቴዎስ ወንጌል 13:39) እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው። (የዮሐንስ ራእይ 12:7) በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥" (መዝሙረ ዳዊት 103:20) ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኃያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ።" (ሮሜ 137) መፈራት ለሚገባው መፈራት፤ ክብር ለሚገባው ክበርን ስጡ፡፡ (ዘጸ.232-22) በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክህን በፊትህ እሰዳለሁ፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፤ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፣ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፣ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፣ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ፣ መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፡፡ (ትንቢተ ዳንኤል 121) በዚያን ዘመን ስለ ህዝብ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያን ዘመን በመፅሐፉ ተፅፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይሆናል፡፡ (የሐዋርያት ስራ 104) እርሱም ትኩር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ፡፡ ጌታ ሆይ፣ ምንድር? ነው አለ፡፡ መልአኩም አለው፡፡ ጸሎትህና ምፅዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ፡፡ (ኦሪት ዘሁልቅ 2231) እግዚአብሔርም የበዓላምን ዓይኖች ከፈተ፤ የእግዚአብሔርን መላዕክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተዘመዘመ ሠይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደ በግንባሩም ወደቀ (መፅሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 514) እርሱም አይደለሁም፤ እኔ የእግዚአብሔር አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና ጌታዬ ለባርያው የሚነግረው ምንድን ነው? አለው፡፡ (ትንቢተ ዳንኤል 8-16-17) በኡባልም ወንዝ መካከል፡፡ ገብርኤል ሆይ፤ ራዕዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ፡፡ አኔም ወደ ቆምኩበት ቀረበ፤ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግንባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም የሰው ልጅ ሆይ፤ ረዕዩን ለፍፃሜው ዘመን እንደሆነ አስተውል አለኝ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

በአዲስ አበባ ጉዳይ ድርድር የለንም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ጋር ባደረገው ውይይት

የአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጎሹ እንዳላማው እና የአብን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ በወቅታዊ ሃ...