Ethiopia G7 “ባልደራስ ትክክል አይመስለኝም” እኔ ዶ ር አብይን አምነዋለው ፕ ሮ ብርሃኑ ነ...
ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ ይሉሃል እንዲህ ነው ጎበዝ!!!!
ኦነግ ኢትዮጵያን ለማፍረሥ ባለው ዓላማ እንዲሁም የአብዛኛው ኦሮሞ በአምሃራው
ላይ ባለው ጥላቻ የአንድነቱን አርበኞች ግ7ን በአሜሪካ ላይ ውሥጣቸው በመግባት ማለትም ኢህአዴግን አብረን እንጣል በሚል ሠበብ
ጎን ለጎን እየሠራ ለማፍረሥ የጀመረውን ሥትራቴጂ አዲሥ አበባ ላይ ከ90% በላይ ያሣካ በሚመሥል ሁኔታ የግንቦት7 ኃላፊን ፕ/ር
ብርሃኑን ነጋን እያጠመቀው መጣ ማለት ይቻላል፡፡ በመጀመሪያም አሜሪካ ላይ ኦነግ በግ7 ውሥጥ ጣልቃ በመግባት ያሉትን አምሃራዎችን
እንዲበሉ፣ በበርሃ የአምሃራ ሠራዊቶች እንዲከዱ በማድረግ ወዘተ… ከፍተኛ እንቅሥቃሤ አደረገ፡፡ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በምርጫ 97
ኢትዮጵያን ለመቀየር ለቅንጅቶች የተሠጣቸውን ዕድል ሢያባክኑ አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ የአዲሥ አበባን ሕዝብ በመክዳት ለኦነጎች
ተንበርክኳል፡፡ ለምን ቢሉ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የአዲሥ አበባን ሕዝብ በመተው የኦነግ ደጋፊ የሆነውን ጠ/ር አብይ አህመድን ሙሉ
ለሙሉ ደግፏል፡፡ የአዲስ አበባ አባት የሆነውን ለአዲሥ አበባ ሕዝብ ዴሞክራሢ እና ሠብዓዊ መብት ሢታገል የነበረውን እሥክንድር
ነጋን ተቃወመ፡፡ ነገር ግን የሚያሣዝነው አቶ የሺዋሥ አሠፋን እና አቶ አንዷለም አራጌን መብላቱም ጭምር ነው የሚያናደው፡፡ ደግሞሥ
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዶ/ር አብይ አህመድን(ኢህአዴግን) ሙሉ ለሙሉ
ከደገፈ እንዴት ታዲያ ፓርቲ ለመመሥረት አሠበ? አንድ ፊቱንሥ ከነሡ ጋር ተጠቃሎ የነሡን ለውጥ ሣይሆን ነውጥሥ የማያሥፈፅምበት
ምክንያት እንዴት ነው? ወይ ከኢህአዴግ ጋር ተጠቃሎ መሥራት አልያም ከፖለቲካው እራሡን ማግለል ይገበዋል፡፡ የኢህአዴግ መንግሥት
ጠ/ር አብይ አህመድ፣ ኦነግ እና ኦፌኮን ሁሉም አንድ ናቸው፡፡ ኦሮሞ ፈርሥት ኢትዮጵያ ትበተን ነው የውሥጥ አጀንዳቸው፡፡ ሥለሆነም
የአንድነት ምሣሌ የሆነው የአዲስ አበባ ሕዝብ ያለው ተሥፋ እሥክንድር ነጋ እና አብን ብቻ ሊሆኑ ነው ማለት ነው፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ላይ ባለው ጥላቻ የአንድነቱን አርበኞች ግ7ን በአሜሪካ ላይ ውሥጣቸው በመግባት ማለትም ኢህአዴግን አብረን እንጣል በሚል ሠበብ
ጎን ለጎን እየሠራ ለማፍረሥ የጀመረውን ሥትራቴጂ አዲሥ አበባ ላይ ከ90% በላይ ያሣካ በሚመሥል ሁኔታ የግንቦት7 ኃላፊን ፕ/ር
ብርሃኑን ነጋን እያጠመቀው መጣ ማለት ይቻላል፡፡ በመጀመሪያም አሜሪካ ላይ ኦነግ በግ7 ውሥጥ ጣልቃ በመግባት ያሉትን አምሃራዎችን
እንዲበሉ፣ በበርሃ የአምሃራ ሠራዊቶች እንዲከዱ በማድረግ ወዘተ… ከፍተኛ እንቅሥቃሤ አደረገ፡፡ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በምርጫ 97
ኢትዮጵያን ለመቀየር ለቅንጅቶች የተሠጣቸውን ዕድል ሢያባክኑ አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ የአዲሥ አበባን ሕዝብ በመክዳት ለኦነጎች
ተንበርክኳል፡፡ ለምን ቢሉ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የአዲሥ አበባን ሕዝብ በመተው የኦነግ ደጋፊ የሆነውን ጠ/ር አብይ አህመድን ሙሉ
ለሙሉ ደግፏል፡፡ የአዲስ አበባ አባት የሆነውን ለአዲሥ አበባ ሕዝብ ዴሞክራሢ እና ሠብዓዊ መብት ሢታገል የነበረውን እሥክንድር
ነጋን ተቃወመ፡፡ ነገር ግን የሚያሣዝነው አቶ የሺዋሥ አሠፋን እና አቶ አንዷለም አራጌን መብላቱም ጭምር ነው የሚያናደው፡፡ ደግሞሥ
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዶ/ር አብይ አህመድን(ኢህአዴግን) ሙሉ ለሙሉ
ከደገፈ እንዴት ታዲያ ፓርቲ ለመመሥረት አሠበ? አንድ ፊቱንሥ ከነሡ ጋር ተጠቃሎ የነሡን ለውጥ ሣይሆን ነውጥሥ የማያሥፈፅምበት
ምክንያት እንዴት ነው? ወይ ከኢህአዴግ ጋር ተጠቃሎ መሥራት አልያም ከፖለቲካው እራሡን ማግለል ይገበዋል፡፡ የኢህአዴግ መንግሥት
ጠ/ር አብይ አህመድ፣ ኦነግ እና ኦፌኮን ሁሉም አንድ ናቸው፡፡ ኦሮሞ ፈርሥት ኢትዮጵያ ትበተን ነው የውሥጥ አጀንዳቸው፡፡ ሥለሆነም
የአንድነት ምሣሌ የሆነው የአዲስ አበባ ሕዝብ ያለው ተሥፋ እሥክንድር ነጋ እና አብን ብቻ ሊሆኑ ነው ማለት ነው፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የፌዴራሊዝም አወቃቀር ሥርዓት እና የፌዴራል ቋንቋ!!!
እና የህብረተሰቡም ንቃተ ህሊና በይበልጥ እንዳደጉት ሀገራት ባብዛኛው በአንድ አይነት አመለካከት ሃገርን በፍትሃዊ እና ሁሉንም
ባማከለ የማሳደግ ባህል ባልጎለበተበት ሃገር በጣም አስፈላጊ እንዲሁም በማህበራዊና በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው
ዕሙን ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአገሪቱን ሪሶርስ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ በፍትሃዊ ለማከፋፈል እና በኢኮኖሚ በይበልጥ እንዲጠቀሙ ለማስቻል
ይረዳል፡፡ ይሁንና አሁን በአገሪቱ ያለው ፌዴራሊዝም አወቃቀሩ ቋንቋን እንደ ዋንኛ መሠረታዊ መዘውር አድርጎ የተዋቀረ ስለሆነ የራሱ
የሆነ አሉታዊ ህፀፆች ይኖሩታል፡፡ ከነዚህም አሉታዊ ህፀፆች ህብረተሰቡን ቀስ በቀስ በዘር እንዲከፋፈል እና በተጨማሪም በቋንቋ
ላይ የተመሠረተው ግዛት ወይም ክልል አቅሙ እንዲሁም የዓስተሳሰብ ብቃቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢኮኖሚ፣ በዲሞክራሲ እንዲሁም በማህበራዊ
ዕድገት እየጎለበተ ሲመጣ ከማን አንሼ የሚል አላስፈላጊ ሃሰብን በመምዘዝ አንዱ ክልል ከሌላው ክልል እርስ በእርሱ እየተቆራቆዘ
የአጠቃላዩን የሃገሪቱን ዕድገት ቀስ በቀስ እያደከመ እንዲመጣ ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን አወቃቀሩ ማለትም የአከላለሉ ሁኔታ በጂኦግራፊ
አቀማመጥ፣ በህብረተሰቡ ማህበራዊ መስተጋብር፣ በቅድመ አሠፋፈር(ታሪክ)፣ ለአስተዳደር በሚመች መልኩ እንዲሁም ህብረተሰቡም በቅርበት
የተሻለ እና ማንኛውንም አገልግሎት ሊያገኝ በሚችልበት መልኩ የተዋቀረ ቢሆን ግን የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከጫፍ ጫፍ እንዲያድግ ከማስቻሉም
በተጨማሪ ህብረተሰቡ በአንድነት የመኖር ባህሉ እየጨመረ እና ያላቸውን አቅም በፍቅር አሟጠው እንዲጠቀሙ ያስችላል፡፡ ሌላው በፌዴራሊዝም
ሥርዓት ከአከላለል ቀጥሎ መታየት ያለበት የአሥተዳደር መዋቅር ሢሆን እሥከ ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ እና ቀበሌ የፌዴራል አሥተዳደር
ሥርዓት ይዘረጋና እና ለክልል፣ ለዞን፣ ለወረዳ እና ለቀበሌ/ከተማ የሚወከሉ አሥተዳዳሪዎችም በህዝብ የተመረጡ የክልሉ፣ የዞኑ፣
የወረዳው እና የቀበሌው/የከተማው ነዋሪዎች እንደየቅደምተከተላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡ ሃገሪቱ ውሥጥ ያሉ አጠቃላይ ከተሞችም አዲሥ
አበባን ጨምሮ ህብረብሔራዊ መልክ ያላቸው እና ባለቤትነታቸውም የነዋሪዎቹ በመሆኑ መተዳደር የሚገባቸው የከተሞቹ ነዋሪ በሆኑ ከንቲባዎች
ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህም የአወቃቀር ሥርዓት የባህልም ሆነ የአሰራር ሥልቶች አንዱ ከአንዱ እንዲወራረሱ በማድረግ በኢኮኖሚው
ላይ የራሱ የሆነ ተጨማሪ አቅም እዲፈጠር ያስችለዋል፡፡ በአጠቃላይ ምንም እንኳን የየክልሉ ቋንቋ የክልሉን ባህላዊ ትውፊቶች ከዘር
ዘር ለማቆየት እና በቋንቋው ላይ ጥናት የሚያደርግ የትኛውም ትውልድ ለግብዓት እንደሚረዳው የማይታበይ ሃቅ ነው፡፡ ሕብረተሠቡም
በተወለደበት ቋንቋ (ማዘር ታንግ) ሊማር ይችላል፡፡ በዚህም የተወለደበት ቋንቋ፣ የፌዴራል ቋንቋ እና ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ በካሪኩለም
ውሥጥ ተቀርፆ ትምህርት ሊሠጥ ይችላል፡፡ የፌዴራል ቋንቋ እና ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ ግን በሁሉም ክልል የግዴታ በካሪኩለም ውሥጥ
መካተት ይኖርበታል፡፡ይሁን እንጂ የክልሌ ቋንቋ ከክልሉ አልፎ ባለው የፌዴራል ቋንቋ በተጨማሪ የፌዴራል ቋንቋ እንዲሆን ግፊት መፍጠር
ግን ከበስተጀርባው አደገኛ የሆነ የዘረኝነት ስልት በህብረተሰቡ እንዲሰርፅ ያደርጋል፡፡ ምክንያቱም ሃገራችን አሁን ካለችበት የዕድገት
ቁመና አንፃር ከአንድ በላይ የፌዴራል ቋንቋ እንዲሆን መመኘት በመላው ሃገሪቱ በሁሉም የስራ ዘርፍ ላይ ቅንጅታዊ አሠራር እንዲሸረሸር፣
አላሥፈላጊ የሥራ ፕሮሠሥ የሚፈጥር፣ የሕብረተሰቡን ጊዜና የሚያባክን እና ለተጨማሪ ወጪ የሚዳርግ እንዲሁም የትርምስ ዓውድ እንዲፈጠር
ከፍተኛ ጫና ከመፍጠሩም በተጨማሪ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በማላሸቅ ያልተገባ ዘውግ ውሥጥ እንዲገባ ያደርገዋል፡፡ የአንድ ሃገር የፌዴራል ቋንቋ የማጆሪቲው አልያም የማይኖሪቲው የህብረተሠብ
ቋንቋ ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን ያለው የአማርኛ የፌዴራል ቋንቋ አንድ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ የጫነው ወይም ለመጨቆን ተብሎ የተፈጠረ
ቋንቋ አደለም፡፡ በአንድ ወቅት ሁሉም የህብረተሠብ ክፍል በአጋጣሚ ያወቁት በመሆኑና ከነፊደላቱ እንዲሁም ካላንደርን ጨምሮ ባገርኛ
የተፈጠረ ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ ይበልጥ ድንቅ ያሥብለዋል፡፡ አለበለዚያግን 84 የብሔረሠብ ቋንቋ አለና ሁሉም እያደጉ ሲመጡ ከማን
አንሼ በሚል ፈሊጥ ተጨማሪ የፌዴራል ቋንቋ እንዲሆን መመኘት ትርምሥ ለመፍጠር ካልሆነ ምንም የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ ለምሳሌ
ብንጠቅስ 1) የትጋራይ ህዝብ ተነስቶ እንደሚታወቀው የግዕዝ ቋንቋ የአገሪቱ የመጀመሪያ ቋንቋ እንደመሆኑ መጠን የትግሪኛም ቋንቋ
ከግዕዙ ጋር ከፍተኛ ዝምድና እና መወራረስ እንዳለው በመጥቀስ ተጨማሪ የፌዴራል ቋንቋ ይሁን የሚል ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ፡፡
2) የአማራ ህዝብም ተነስቶ የአማራው የአማርኛ ቋንቋ ከግዕዙ በውርስ የተገኘ በመሆኑ ከነዘዬው ተጨማሪ የፌዴራል ቋንቋ ይሁን የሚል
ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ፡፡ 3) የኦሮሞ ህዝብም የኦሮምኛ ቋንቋ ከክልሉ የህዝብ ብዛት ከሌላው ክልል ህዝብ ብዛት አንፃር ስለሚበልጥ
ተጨማሪ የፌዴራል ቋንቋ ይሁን የሚል ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ፡፡ ሌላም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ስለሆነም የክልል ቋንቋ የክልሉን ባህል
ለመጠበቅ እና ለመመርመር ካልሆነ በቀር በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የፌዴራል ቋንቋ አያስፈልጋትም፡፡ ምክንያቱም
እንኳን የስራ ቋንቋ ተቀይጦ ይቅርና አበው እንደሚሉት እንኳን ዘንቦብሽ እንዲሁም ጤዛ ነሽ ይሆናል ነገሩ፡፡ ስለሆነም የፌዴራል
አወቃቀርን በተመለከተ የኢህአዴግ ሥርዓት ከመምጣቱ በፊት 14 ክልሎች የነበሩት ሲሆን ሸዋ፣ ጎጃም፣ ቤጌምድር፣ ከፋ፣ ትግሬ፣ ኤርትራ፣
ወሎ፣ ሃራርጌ፣ ወለጋ፣ ኢሊባቡር፣ ጋሞጎፋ፣ አሩሲ፣ ባሌ፣ ሲዳሞ ተብለው ይጠሩ የነበረ እና የራሳቸውም የሆነ ወሠን ወይም ድንበር
ነበራቸው፡፡ ይሁን እንጂ በኢሕአዴግ ሥርዓት ተለውጦ ቋንቋን እና ብሔርን መሠረት አድርጎ እንደገና የተዋቀረ ሢሆን ክልሎቹም አማራ፣
ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሃራሪ፣ ድሬዳዋ፣ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሊ ተብለው እንደ አዲሥ ከብሔር እና ከቋንቋ ጋር
የተያያዘ የክልል ሥሞች እንዲሠየሙና የራሳቸው የሆነ ወሠን ወይም ድንበር እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፡ በኢህአዴግ ሥርዓት ግን በምን
መሥፈርት እንዲሁም በማን ውሣኔ ይህ አዲሥ የክልል አከፋፈል እንደተደረገ ባለውቅም ብሔር እና ቋንቋን መሠረት ያደረገ በመሆኑ ግን
ከፍተኛ መሠረታዊ ችግር እንዳለው ግልፅ እና ግልፅ ነው፡፡ በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ አዲሦቹ ክልሎች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በባህላዊ
እየጎለበቱ ሢመጡ አሉታዊ ደሃራው ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ መገመት አያዳግትም፡፡ ሥለሆነም ህገመንግሥቱ ሠው ሠራሽ እስከሆነ
ድረስ ዴሞክራሢያዊ ምርጫ በማከናወን እና በነዚህም በሕዝብ በተመረጡ ሠዎች አማካይነት ቋንቋና ብሔርን ወደ ጎን በመተው በጥልቀት
በመፈተሸ እና እርምት በመውሠድ መሻሻል ይኖርበታል፡፡ በተለይም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ለምሳሌ ሸዋ በአጠቃላይ አማራውም፣ ትግሬውም፣
ጉራጌውም፣ ወላይታውም፣ ኦሮሞውም፣ ሃረሬውም፣ ሶማሌውም፣ ጋምቤላውም፣ ቤንሻንጉሉም፣ አፋሩም የሚኖርበት በመሆኑ እራሡን ችሎ እንደ
አንድ ክልል በማድረግ ርዕሠ መቀመጫውን የአገሪቱ ካፒታል ዋና ከተማ በሆነችው በአዲስ አበባ ላይ እንዲሆን ማድረግ፡፡ ሌላው አማራጭ
ደግሞ ለምሣሌ በለገጣፎ መሥመር ያለውን ወረዳ ወደ አምሃራ ክልል እዲጠቃለል እና የአዲሥ አበባን ቦርደር እንዲጋራ ማድረግ፣ በቡታጅራ
መሥመር ላይ ያሉትን ወረዳዎች ወደ ደቡቡ ክልል እንዲጠቃለሉ እና የአዲሥ አበባን ቦርደር እንዲጋሩ ማድረግ እንዲሁም በወለጋ መሥመር
ያሉ ወረዳዎች እንደተጠበቁ በኦሮሚያ ክልል እንዲሆኑ በማድረግ ሦሥቱም የአዲሥ አበባን ቦርደር እንዲጋሩ እና ማህበራዊ ኑሯቸው እንዲጎለብት
ማድረግ ይቻላል፡፡ ሌሎቹንም በጥልቀት ጥናት በማድረግ በጂኦግራፊ አቀማመጥ፣ በህብረተሰቡ ማህበራዊ መስተጋብር፣ በቅድመ አሠፋፈር(ታሪክ)፣
ለአስተዳደር በሚመች መልኩ እንዲሁም ህብረተሰቡም በቅርበት የተሻለ እና ማንኛውንም አገልግሎት ሊያገኝ በሚችልበት መልኩ በማድረግ
በተጨማሪም የአብዛኛውን የሕብረተሠቡን ፍላጎት ቅድሚያ በመሥጠት በገለልተኛ አካል በፌዴራልም አማካይነት ወደ ተፈለገው ወረዳ እና
አሥተዳደር በማጠቃለል ክልሎቹንም የብሔር ሥም ከመሥጠት በመቆጠብ መፍትሔ መሻት ግድ ነው፡፡ ሌላው ለፌዴራሊዝም አወቃቀር ይበልጥ
መጠናከር የህገመንግሥቱን አንቀፅ 39 እራስን በራስ መወሠን እሥከመገንጠል የሚለው በድብቅ ወይም በጀርባ የራሥን ክልል የሚጠናከርበት
እና ከሌላው ለራስ በማድላት በተለያየ ሲስተም ክልሉ የሚጠቀምበትን ዘዴ በመዘየድ ሁኔታው ሲያመች የመገንጠል አዝማሚያ ብሂል ሥላላት
ህገ መንግሥቱ መሻሻል ይኖርበታል፡፡ ምንም እንኳን አሁን የዘረኝነት መንፈስ በአገራችን ኢትዮጵያ ባልጠፋበት ወቅት ህገ መንግስቱን
ማሻሻል በተቃራኒው መጠነኛ የሆኑ አንዳንድ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊኖሩት እንደሚችል የሚታወቅ ቢሆንም የተሻለን ለመፍጠር ግን ማሻሻያ
መውሠዱ ጊዜ የማይሠጥ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን በቋንቋ ላይ እና በሌሎች ጉዳዮች ከዘረኝነት ጋር ሊነሱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ
ዳግም እንዳይቀለበስ የፌዴራል አወቃቀር ላይ ከላይ በገለፅኩት መልኩ መንግስት በጥልቀት በመፈተሽ ተፅኖውን ማርገብ ይጠበቅበታል፡፡
ሠላም በምድራችን ይስፈን!!!
Comments
Post a Comment