Menagesha Amba Mariam and Gara Medanialem Andinet Gedam



እመቤታችን ድንግል ማርያም አብ የመረጣት የወልድ ማደሪያ አማላጃችን ናት!!!!!!!!!!!!!

ስለድንግል ማርያም፡- (የሉቃስ ወንጌል 1:28) መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፤ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፤ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። (የሉቃስ ወንጌል 1:35) መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። (ኢሳያስ 49፡23) ነገስታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፣ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግምባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፣ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፣ እኔንም በመተማመን የጠበቁ አያፍሩም፡፡ (ኢሳያስ 60፡14) የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፣ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፣ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል፡፡ (የዮሐንስ ወነጌል 2፡1-10) የወይን ጠጅ ባለቀ ጊዜ የየሱስ እናት፤ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው፡፡……ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፤ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፣ አነተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስካሁን አቆይተሃል አለው፡፡ (የሉቃስ ወንጌል 1:48) የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፡፡ (የሉቃስ ወንጌል 1:41) ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፡፡ (መኃልዬ መኃልዬ ዘሰለሞን 4፡15) አንቺ የገነት ምንጭ፤ የሕይወት ውኃ ጉድጓድ፣ ከሊባኖስ የሚፈስ ወንዝ ነሽ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

Asrat Breaking News! የባለ አደራ ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ታገደ

www.danyboyrpda.cf