ሥለሕዝብ እና ቤት ቆጠራ!!!

እንዴት የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ሕዝቡ ከማንነት እና ከአሥተዳደር ወሠን ጋር ማያያዝ የለበትም ይባላል። ለዛውም ከብሔራዊ ሥታሥቲክሥ ኃላፊ። ምንአልባት ኃላፊው ኦሮሞ ሥለሆኑ የራሥን ጥቅም ለማሥጠበቅ ካልሆነ በቀር። ጥቅሙ ደግሞ ዘርፈ ብዙ ነው። በየክልሎች ለሚውል ለሀብት ክፍፍል(የመብራት ሽፋን፣ የውሃ አቅርቦት ሽፋን፣ የቴሌኮም ሽፋን፣ የመንገድ ሽፋን፣ ለጤና አገልግሎት ሽፋን፣ ለትምህርት ሥርጭት ሽፋን፣ ለኢንቨሥትመንት ሽፋን፣ ለግብርና ሽፋን፣ ለትራንሥፖርት አገልግሎት ሥርጭት ሽፋን፣ ወዘተ...)፣ ለክልል በጀት ድልድል፣ ለኤንጂኦ እርዳታ ጥናት፣ ለውጭ ሀገር ብድር፣ ለሕዝብ ተወካይ(ለምርጫ)፣ ለገቢዎች፣ ለተለያዩ የንግድ ጥናቶች፣ ለተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች በየዕምነቶቻቸው ወዘተ... መዘርዘር ይቻላል። ሥለሆነም አዲሡ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ሢካሄድ በየትኛውም ቦታ ተፈናቅለው ያሉ ሢቆጠሩ አሁን ያሉበት ቦታ ጊዜያዊ እሥከሆነ ድረሥ በፊት በነበሩበት ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ እና ቀበሌ ሥም መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ሌላው በዳታ አሠባሠብ ላይ ተፈናቃይ መሆናቸውን የሚገልፅ እንዲሁም ከየት ወዴት ተፈናቅለው እንደመጡ የሚዘረዝር መጠይቅ ሊኖር ይገባል፡፡ በመጨረሻም የነዚህ ሕዝብ ብዛት ቀድሞ በነበሩበት ክልል ላይ የሚደመር ይሆናል፡፡ ይህም ከየትም ቦታ ወደ ተፈለገው ቦታ በማፍለሥ የተፈለገን የቦታ የህዝብ ብዛት ዲሞግራፊ ሊቀይሩ የሚወጥኑትን ውጥን ያመክናል፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

Comments

Popular posts from this blog

Asrat Breaking News! የባለ አደራ ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ታገደ

www.danyboyrpda.cf