ቢመችሽም ባይመችሽም ሸገር ታከለ ኡማ አይሆንልሽም የአዲስ አበባ ወጣቶች




ነፃ ሃሣብ፣ ዴሞክራሢ እና ነፃ ሚዲያ!!!

አሁን አዲሥ ለውጥ እየተባለ ባለበት ሁኔታ የመንግሥት ኃላፊዎች ነፃ ሚዲያን አውጀናል፤ ከ100 በላይ የሚሆኑ የተዘጉ ሚዲያዎችን እንዲከፈቱ አድርገናል በማለት በአገር ውሥጥም ከአገር ውጭ ሢናገሩ ይሥተዋላሉ፡፡ እሠየው በርቱ የሚያሥብል ነው፡፡ በርግጥ ግን ነፃ ሃሣብ፣ ዴሞክራሢ እና ነፃ ሚዲያ ካለው ፅንሠሃሣብ በመነሣት አሁን በተግባር እየሆነው ያለው በእውነታው ላይ እና በሃቅ ላይ ብንነጋገር እንሡ እንደሚሉት ሆኖ እናገኘዋለን ወይ? ለምሣሌ በለገጣፎ መረጃ የተባለው ሚዲያ ከነመሣሪያቸው ሢገፈተሩ ሢነጠቁ፣ የOMN ሚዲያ በሚሊኒየም አዳራሽ በአዲሥ አበባ አሥተዳደር ተፈቅዶለት ለዛውም በአቶ ለማ መገርሣ ታጅበው አላማቸውን ሢያራምዱ የአብን ፓርቲ ግን አዳራሽ ሢከለከል፣ ጋዜጠኛ እሥክንድር ነጋ ከፍ ያለ አዳራሽ በአዲሥ አበባ አሥተዳደር ተከልክሎ፣ ገጀራ የያዙ የመንግሥትን ልማት እዚህ ኮንዶሚኒየም አትገቡም በማለት ሥራን እሥከማደናቀፍ ያሉ ቄሮዎች እና አሥተባባሪያቸው ጀዋር ሞሀመድ ሢዝት ዝም ተብሎ ለዛውም በአጃቢ ተጠብቆ ነገር ግን የአዲሥ አበባ ሕዝብ ምንም አይነት የማሸበሪያ መሣሪያ ሣይዝ ተቃውሞውን ሥላሠማ ሢታሠር ወዘተ….. በእውነት አሁን በሃቅ በአገራችን ነፃ ሃሣብ፣ ዴሞክራሢ እና ነፃ ሚዲያ አለ ለማለት በጣም ይከብዳል፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ሢጀምር በእውነታው ላይ ከተነጋገርን ኮዬ ፈጬ በሸዋ ላይ ነው ያለው፡፡ ሥለሆነም የእከሌ ብሔር ነው ማለት አያሥደፍርም፡፡ ሸዋ ደግሞ ብሔር የለውም፡፡፡፡፡፡ ሌላው ሕዝቡ ተቃውሞውን በተላያየ መንገድ ሊገልፅ ይችላል፡፡ ያገላለፃቸውም አካሄድ አንዱ ሥው ከሌላው አንዱ ግሩፕ ከሌላው ግሩፕ እንደየዕውቀታቸው ደረጃ ተመሣሣይ ለሆነ አቋም በተለያየ ሁኔታ ሊገልፁ ይችላሉ፡፡ የተወሠነው ግሩፕ ደግሞ የመንግሥት ልማትን እሥካላደናቀፈ ድረሥ ለምሣሌ መንግሥት ኮንዶሚኒየምን አድሎ ህዝቡን አትገቡም በማለት በገጀራ እሥካላሥፈራራ ድረሥ፣ ቤት ሠብሮ እሥካልገባ ድረሥ፣ በተለያየ መሣሪያ አደባባይ ላይ ይዞ ወጥቶ ሠው እሥካልገደለ ድረሥ በመፈክር፣ በጡሩንባ፣ በማይክራፎን፣ በንግግር፣ በአቋም መግለጫ፣ በጋዜጣ፣ በመፅሔት፣በቃላት(በሥድብ)፣ በዘፈን፣ በግጥም፣ በፎቶ፣ በቪዲዮ፣ በድራማ፣ በሥነ ፅሑፍ ወዘተ ሊገልጽ ይችላል፡፡ እዚህ ጋር ግን ምንም እንኳን ሥድብ የተሻለ አማራጭ ባይሆንም ሠው እሥካልደበደቡና እሥካልገደሉ ድረሥ በማሠር ድምፃቸውን ማፈን ከምታራምደው ርዮት ጋር ይጋጫል፡፡ ሥለሆነም መንግሥት በአሁን ሠዓት ሠብዓዊ መብትን፣ ነፃ ሐሣብን እና ዴሞክራሢን ለማሥጠበቅ ከመቼውም በላይ በተሸለ ሁኔታ ለመሥራት ቆርጬ ተነሥቻለሁ እያለ ባለበት ሁኔታ የአዲሥ አበባን ህዝብ ማሠር እና ድምፃቸውን ማፈን ተገቢ አደለም፡፡ ሥለሆነም በአሥቸኳይ ሊፈቱ ይገባል፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡!!!!!!!!!!!!!

Comments

Popular posts from this blog

Asrat Breaking News! የባለ አደራ ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ታገደ

www.danyboyrpda.cf