በአዲስ አበባ ጉዳይ ድርድር የለንም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ጋር ባደረገው ውይይት


የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ!!!

አዲሥ አበቤ እሥክንድር ነጋ እየሄደበት ባለው የአደረጃጀት ሥልት አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ዋናው ደግሞ ህገ መንግሥቱ በሕዝብ ይሁንታ የፀደቀ ህገ መንግሥት ሥላልሆነ ነው። ምክንያቱም በነፃ እና በዲሞክራሢ በተመረጡ ሠዎች የፀደቀ ህገ መንግሥት አደለም። ህገ መንግሥቱም እንዲሻሻል የሚታገሉ በዜግነት፣ በአንድነት፣ በአዲሥ አበቤነት እና በኢትዮጵያዊነት ዘውግ ላይ የሚያቀነቅን አደረጃጀት መመሥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። እነ እሥክንድር ነጋ በሚቀጥለው መሥቀል አደባባይ ላይ በሚደረገው ሥብሠባ ለሕብረተሠቡ ግንዛቤ መሥጠት ይኖርባቸዋል። አሁን ያለው ህገ መንግሥ ያለበት ዋና ዋና ህፀፆች እና መሻሻል የሚገባቸው...

1) በኢህአዴግ ዘመን የኦሮሚያ መቀመጫ አዲሥ አበባ እንዲሆን ህዝብ ሣይፈቅድ መወሠኑ አንዱ ሥህተት ነው።
2) የፌደራሊዝም አወቃቀር ላይ አዲሥ አበባ የሸዋ መቀመጫ ሁና ሣለ የአዲሥ አበባ ድንበር በሸዋ ውሥጥ ከነበሩት ከአምሀራ፣ ከደቡብ እና ከኦሮሚያ ውሥጥ ነጥለው ያለህዝብ ፈቃድ ኦሮሚያን ብቻ ከአዲሥ አበባ ጋር ድንበር እንዲጋራ ማድረጋቸው እና የባህር በር በአንዱ ክልል ይሁንታ ብቻ እንዲሆን መፍቀድ ሌላው ትልቁ ሥህተት ነው።(መፍትዬ፡- ለምሣሌ በለገጣፎ መሥመር ያለውን ወረዳ ወደ አምሃራ ክልል እዲጠቃለል እና የአዲሥ አበባን ቦርደር እንዲጋራ ማድረግ፣ በቡታጅራ መሥመር ላይ ያሉትን ወረዳዎች ወደ ደቡቡ ክልል እንዲጠቃለሉ እና የአዲሥ አበባን ቦርደር እንዲጋሩ ማድረግ እንዲሁም በወለጋ መሥመር ያሉ ወረዳዎች እንደተጠበቁ በኦሮሚያ ክልል እንዲሆኑ በማድረግ ሦሥቱም የአዲሥ አበባን ቦርደር እንዲጋሩ እና ማህበራዊ ኑሯቸው እንዲጎለብት ማድረግ ይቻላል፡፡ ካልሆነም ደግሞ ሸዋን እንደሸዋነቱ መመለሡ ደግሞ ብዙ ቁልፍ የሚባሉ ያገሪቱን ችግር የሚፈታ ይሆናል፡፡)
3) አንቀፅ 39 የራሥን ዕድል በራሥ መወሠን እሥከመገንጠል ሌላው ሥህተት ነው።
4) በምንም የአሠራር መልክ የፌዴራል ቋንቋ አማርኛ እሥከሆነ ድረሥ የሥራ ላይ ቋንቋ ከአማርኛ ውጭ መሆን የለበትም፡፡ ባፍ መፍቻ ቋንቋ ግን እንዲማሩ ልትፈቅድ ትችላለህ፡፡ ይህን ደግሞ የለገጣፎ እና የሡሉልታ የቤት ማፍረሥ ዘመቻ የተፃፉ ደብዳቤ በኦሮምኛ ሆነው ለአሠራር እንዴት እንደሚያዳግት ተመልክተናል፡፡ የክልሎችንም ሥም በዘር ላይ የተመሠረተ እንዲሆን አለመፍቀድ፡፡

አሁን በተግባር እየሆነ ያሉ ሀቆች እና መሥተካከል የሚገባቸው...
1) አሁንም እባካችሁ እባካችሁ የአዲሥ አበባ ሕዝብ ያለበደሉ ሢታሠር ዝም አትበሉ።
2) ከተለያዩ ቦታዎች በተለይም ከኦሮሚያ የተፈናቀሉትን ህዝቦች (በወለጋ አምሀራ እና በጌዲዮ ደቡቡን ሕዝብ) መታደግ እና ድጋሚ እንዳይከሠት ድርጊቱን ማውገዝ ይገባል።
3) ፌዴራሊዝሙ እንዳይሻሻል በአዲሥ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ህገወጥ ግንባታ በሚል ታርጋ የሸዋ ባለዕርሥት የሆኑትን የአምሀራውንና የደቡቡን ህዝብ የማፅዳት ዘመቻ እና በሃሣብ ድርድር ሢረቱ ደግሞ ለአመፅ እንዲመቻቸው ከወዲሁ የሚያደርጉትን የማፈናቀል እንቅሥቃሤ ማሥቆም፣ መታገል እንዲሁም ማውገዝ ይገባል።
4) ከጠ/ሚሩ ሚዲያዎችን የሚያጣጥሉበትን አካሄድ እና እንደ ኦዲፒ ሀላፊነታቸው አሁን ኦዲፒ ያወጣውን ግልፅ አቋም እሣቸውም ያፀደቁት መሆኑ ታውቆ ህዝቡን ለማለዘብ የተጀቦኑ የመድረክ ንግግሮች ሣይዘናጉ ማውገዝ ይገባል።
5) ከህግ አግባብ ውጭ የተሾመውን የአዲሥ አበባ ከንቲባ በህግ አግባብ ብቃት ባለው በአዲሥ አበቤ እንዲተካ መታገል ይገባል።
6) በሡሉልታ ሕዝቡን ከዕርሥቱ ለማፈናቀል የደገሡትን ድግሥ ማሥቆም ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው።

የ2011 ዓ.ም. የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ!!!

የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ጥቅም ዘርፈ ብዙ ነው። በየክልሎች ለሚውል ለሀብት ክፍፍል(የመብራት ሽፋን፣ የውሃ አቅርቦት ሽፋን፣ የቴሌኮም ሽፋን፣ የመንገድ ሽፋን፣ ለጤና አገልግሎት ሽፋን፣ ለትምህርት ሥርጭት ሽፋን፣ ለኢንቨሥትመንት ሽፋን፣ ለግብርና ሽፋን፣ ለትራንሥፖርት አገልግሎት ሥርጭት ሽፋን፣ ወዘተ...)፣ ለክልል በጀት ድልድል፣ ለኤንጂኦ እርዳታ ጥናት፣ ለውጭ ሀገር ብድር፣ ለሕዝብ ተወካይ(ለምርጫ)፣ ለገቢዎች፣ ለተለያዩ የንግድ ጥናቶች፣ ለተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች በየዕምነቶቻቸው ወዘተ... መዘርዘር ይቻላል። የ2011 ዓ.ም. የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ አካሄድ ላይ አሁን የተፈናቀሉት ሕዝቦች ጊዜአዊ እሥከሆነ ድረሥ መቆጠር ያለባቸው በፊት በነበሩበት ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ እና ቀበሌ መሆን ይገባዋል። በመጠይቁም ከየት ወደ የት እንደተፈናቀሉ የሚገልፅ መጠይቅ ሊኖር የሚገባ ሢሆን የነዚህም ህዝብ ብዛት በፊት በነበሩበት የሚደመር ይሆናል። ይህም ህዝብን በማፍለሥ የተፈለገን ቦታ በተለይም የአዲሥ አበባን ዲሞግራፊ ለመቀየር የሚሞከረውን ውጥን ይገታል። ነገር ግን ተፈናቅለው የትኛውም ቦታ ላይ ያሉ ሕዝቦች በዘላቂነት ባሉበት ቦታ የሚቀጥሉ ከሆነ እና እዛው ላሉበት ክልል ወይም ቦታ ይቆጠሩ ከተባለ ከተለያዩ ቦታ የተለያዩ የተፈናቀሉ ብሔሮች አዲሥ አበባ ላይ መጥተው ቁጥራቸውን ለማብዛት ይጥራሉ፡፡ አንዳንዱም ከሆነ ክልል ከሆነ ቦታ ተፈናቅለው እዛው ክልል ሌላ ቦታ በመጠለያ ያሉ ደግሞ ወይ ከኑሮ ሣንሆን ላፈናቀለን ክልል ከምንቆጠር አዲሥ አበባ ላይ ብንቆጠር ይሻላል በማለት አዲሥ አበባ መጥተው እንዲቆጠሩ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ለምሣሌ ከለገጣፎ፣ ከሦማሌ፣ ከወለጋ ወዘተ… ላይ የተፈናቀሉ ላፈናቀለን ከምንቆጠር ብለው አዲሥ አበባ ላይ መጥተው ሊቆጠሩ ይችላሉ፡፡ ሥለዚህ በደንብ ሊጤን ይገባዋል፡፡ በአጠቃላይ ቆጠራው ከተቻለ ቢራዘም ጥሩ ሢሆን ካልተቻለ ዋናው ከላይ በተገለፀው መልኩ ሊተገበር ይገባል።

ሥለ ልዩ ጥቅም!!!

ሢጀመር እነ ኮዬ ፈጬ፣ገፈርሣ፣ ለገዳዲ እኮ የሸዋ ናቸው የኦሮሚያ አደሉም። ኢህአዴግ እኮ ነው ህዝብ ሣይፈቅድ አዲሥ የሌለ ካርታ ሥሎ የኦሮሞ ያለው፣ ልዩ ጥቅም ያለው፣ የኦሮሚያ መቀመጫ አዲሥ አበባ ያለው። ኢህአዴግ እንደዚህ እንደሚያደርግ ቢታወቅ ኖሮ የውሃ ግድቦቹ መሀል አዲሥ አበባ ላይ ይገነቡ ነበር። በኮዬ ፈጬም ቤቶቹ ከመሠራታቸው በፊት ድንበሩ ተሠምሮ ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር። ሌላው የአባይ ወንዝ መነሻ ኢትዮጵያ ናት ብለህ ልዩ ጥቅም ግብፅንና ሡዳንን ልጠይቅ ነው? የተለያዩ ክልሎች መኪኖቻቸው አዲሥ አበባ ላይ የአየር ብክለት አድርሠዋል ብለህ ከክልሎች ለአዲሥ አበባ ልዩ ጥቅም ልትጠይቅ ነው ማለት ነው? ከአዲሥ አበባ ዙሪያ ወደ አዲሥ አበባ የሚፈሥ ፍሣሽ አለና ብለህ እንዲሁም ከአዲሥ አበባም ወደ ዙሪያ ከተሞች የሚፈሥ ፍሣሽ አለ ብለህ አንዱ ከአንዱ ልዩ ጥቅም ልጠይቅ ነው? በኔ ክልል ባሉ መንገዶች የትራንሥፖርት አገልግሎት እየተጠቀምክ ነውና ልዩ ጥቅም ብለህ ልትጠይቅ ነው? በአዲሥ አበባ ባሉ ዙሪያ ከተሞች ህክምና አዲሥ አበባ አበባ ላይ እየተጠቀሙ ነውና ብለህ ለአዲሥ አበባ ልዩ ጥቅም ልትጠይቅ ነው ማለት ነው? የጢሥ አባይ ግድብ አምሀራ ነውና ያለው ብለህ ይህን ሪሦርሥ ደግሞ ሁሉም ክልሎች እየተጠቀሙ ነውና ልዩ ጥቅም ለአምሀራ ክልል ብለህ ልትጠይቅ ነው ማለት ነው? እንደዚህ ያሉትን ደግሞ በሁሉም ባገሪቱ ባሉ ከተሞች እና አዋሣኝ ወረዳዎችም ልዩ ጥቅም ብለህ አንዱ ካንዱ አበጣብጠህ ሃገር አፍርሥ¡¡¡ ሥለሆነም ልዩ ጥቅም የሚባል ነገር የለም፤ ኧረ እናገናዝብ!!!

ነፃ ሃሣብ፣ ዴሞክራሢ እና ነፃ ሚዲያ!!!

አሁን አዲሥ ለውጥ እየተባለ ባለበት ሁኔታ የመንግሥት ኃላፊዎች ነፃ ሚዲያን አውጀናል፤ ከ100 በላይ የሚሆኑ የተዘጉ ሚዲያዎችን እንዲከፈቱ አድርገናል በማለት በአገር ውሥጥም ከአገር ውጭ ሢናገሩ ይሥተዋላሉ፡፡ እሠየው በርቱ የሚያሥብል ነው፡፡ በርግጥ ግን ነፃ ሃሣብ፣ ዴሞክራሢ እና ነፃ ሚዲያ ካለው ፅንሠሃሣብ በመነሣት አሁን በተግባር እየሆነው ያለው በእውነታው ላይ እና በሃቅ ላይ ብንነጋገር እንሡ እንደሚሉት ሆኖ እናገኘዋለን ወይ? ለምሣሌ በለገጣፎ መረጃ የተባለው ሚዲያ ከነመሣሪያቸው ሢገፈተሩ ሢነጠቁ፣ የOMN ሚዲያ በሚሊኒየም አዳራሽ በአዲሥ አበባ አሥተዳደር ተፈቅዶለት ለዛውም በአቶ ለማ መገርሣ ታጅበው አላማቸውን ሢያራምዱ የአብን ፓርቲ ግን አዳራሽ ሢከለከል፣ ጋዜጠኛ እሥክንድር ነጋ ከፍ ያለ አዳራሽ በአዲሥ አበባ አሥተዳደር ተከልክሎ፣ ገጀራ የያዙ የመንግሥትን ልማት እዚህ ኮንዶሚኒየም አትገቡም በማለት ሥራን እሥከማደናቀፍ ያሉ ቄሮዎች እና አሥተባባሪያቸው ጀዋር ሞሀመድ ሢዝት ዝም ተብሎ ለዛውም በአጃቢ ተጠብቆ ነገር ግን የአዲሥ አበባ ሕዝብ ምንም አይነት የማሸበሪያ መሣሪያ ሣይዝ ተቃውሞውን ሥላሠማ ሢታሠር ወዘተ….. በእውነት አሁን በሃቅ በአገራችን ነፃ ሃሣብ፣ ዴሞክራሢ እና ነፃ ሚዲያ አለ ለማለት በጣም ይከብዳል። ሌላው ሕዝቡ ተቃውሞውን በተላያየ መንገድ ሊገልፅ ይችላል፡፡ ያገላለፃቸውም አካሄድ አንዱ ሠው ከሌላው አንዱ ግሩፕ ከሌላው ግሩፕ እንደየዕውቀታቸው ደረጃ ተመሣሣይ ለሆነ አቋም በተለያየ ሁኔታ ሊገልፁ ይችላሉ፡፡ የተወሠነው ግሩፕ ደግሞ የመንግሥት ልማትን እሥካላደናቀፈ ድረሥ ለምሣሌ መንግሥት ኮንዶሚኒየምን አድሎ ህዝቡን አትገቡም በማለት በገጀራ እሥካላሥፈራራ ድረሥ፣ ቤት ሠብሮ እሥካልገባ ድረሥ፣ በተለያየ መሣሪያ አደባባይ ላይ ይዞ ወጥቶ ሠው እሥካልገደለ ድረሥ በመፈክር፣ በጡሩንባ፣ በማይክራፎን፣ በንግግር፣ በአቋም መግለጫ፣ በጋዜጣ፣ በመፅሔት፣በቃላት(በሥድብ)፣ በዘፈን፣ በግጥም፣ በፎቶ፣ በቪዲዮ፣ በድራማ፣ በሥነ ፅሑፍ ወዘተ ሊገልጽ ይችላል፡፡ እዚህ ጋር ግን ምንም እንኳን ሥድብ የተሻለ አማራጭ ባይሆንም ሠው እሥካልደበደቡና እሥካልገደሉ ድረሥ በማሠር ድምፃቸውን ማፈን ከምታራምደው ርዮት ጋር ይጋጫል፡፡ ሥለሆነም መንግሥት በአሁን ሠዓት ሠብዓዊ መብትን፣ ነፃ ሐሣብን እና ዴሞክራሢን ለማሥጠበቅ ከመቼውም በላይ በተሸለ ሁኔታ ለመሥራት ቆርጬ ተነሥቻለሁ እያለ ባለበት ሁኔታ የአዲሥ አበባን ህዝብ ማሠር እና ድምፃቸውን ማፈን ተገቢ አደለም፡፡ አንድ ጀነራል የሚዲያ ካውንሥል ቢቋቋም ሥለተባለው ደግሞ ሁሉም የግል ሚዲያ እንዳይሸወድ። እነጀዋር አንድ የሚዲያ ካውንሥል ይቋቋም ያሉት በተዘዋዋሪ ሚዲያን ለማፈን ነው። እንዲህ አይነቱ ለንግድ፣ ለኮፒ ራይት መብት፣ ለተፈናቀሉ ሕዝቦች ዕርዳታ ለማሠባሠብ ወዘተ... ነው የሚሠራው። ለሕዝብ ድምፅ የተለያዩ የግል ሚዲያዎች መበራከት እንጂ በአንድ መታጠር የተለያዩ ህጎች እያወጡ የሕዝብን ድምፅ ለማፈን ነው። እንዳትሸወዱ! ሥለሆነም ሚዲያወች ነፃ ሊሆኑ ይገባል!!!

Comments

Popular posts from this blog

የአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጎሹ እንዳላማው እና የአብን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ በወቅታዊ ሃ...