ESAT Day Celebrity with Getsh Mamo እነ መሳይ መኮንን በጌትሽ ማሞ ሙዚቃ በስሜት ሲጨፍሩ ...


ቀን 06/11 2010 ዓ.ም.
ኢትዮጵያዊው ሙሴ!
ወትሮም የነበርን በእርሱ የተፈጠርን
ሀገረ እግዚአብሔር ብርቱዎች ሃያላን
እስራኤል-ኢትዮጵያ ቀድሞም የባረከን
የእስራኤል ርዕስት የከነዓን ምድር
የኢትዮጵያ ፈርጥ ደሞም የባህር ዳር
ጊዎን የሚከባት የኖህ መቀመጫ የበረከት ሀገር
እንዴት ትረሳለች
እንደምን ታልፋለች
እንዴት ትተዋለች
እንዴት ትመክናለች
እጆቿን ዘርግታ ፈጣሪዬ ያለች፡፡
ታዲያ ሙሴን ለእስራኤል ከግብፁ ባርነት
ዮርዳኖስን ከፍሎ ነፃ እንዳወጣቸው ከሞት ከአርነት
እምዬን ኢትዮጵያ ደግሞ ሊደርስላት
ብረሳሽ ቀኜ ይርሳኝ አለሁልሽ ሊላት
ኢትዮጵያዊውን ሙሴ ኢትዮጵዊ አርበኛ
እኔን ቢያስነሳላት ቢያደርግ ጥበበኛ
ማን ይቃወመዋል
ማንስ ይችለዋል
አስተውል አትቅና እመነኝ እመነኝ
መቀበል ብቻ ነው አርያ እንድሆን እርሱ ከመረጠኝ፡፡
በእርግጥ እናውቃለን ማጉረምረም መዘንጋት እየተዋለለ
ዮርዳኖስ ተሻግሮ የግብፅ ፍርፋሪ መመኘት እንዳለ፡፡
ይሁን እንጂ ቅሉ የጉዞአችን መስመር
መድረሻ ስላለው የከንዓን ርዕስት የከነዓን መንደር
መቁሰሉ መድማቱ
ዝቅታም ስላለ ከፍ እንደማለቱ
መውውጣቱ መውረዱ
እየተገፋፉ ወደፊት መሄዱ
ከነዓን ለመውረስ
እራስን በማደስ
ይኸው ነው ሚስጥሩ የሚያስጨንቀው ምጥ
ለመውጣት ለማምለጥ
ከጭቃው ረመጥ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

በአዲስ አበባ ጉዳይ ድርድር የለንም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ጋር ባደረገው ውይይት

የአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጎሹ እንዳላማው እና የአብን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ በወቅታዊ ሃ...